ስታርት አፕ ምንድ ነው?

ስታርት አፕ ሲባል ማንኛውም በአነስተኛ ደረጃ የተጀመረ የሥራ መስክ ማለት አይደለም ስታርት አፕ ሐሳብ በፈጠራ ሐሳብ (ኢኖቬቲቭ አይዲያ )ቴክኖሎጂን ተንተርሶ አንድን ችግር ለመፍታት የሚቋቋም ዘር ማለት ነው፡፡

ቴክኖሎጂን ካልተጠቀመ የፈጠራ ሐሳብ ከሌለ እና የሚፈታው ችግር ከሌለ ሥራ መጀመር ብቻ ስታርት አፕ አያስብለውም፡፡

ስታርት አፕ ማለት ይሄ ነው ካልን በኋላ ግን ይሄ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይም አዲስ ቋንቋ ነው ከቴክሎጂ ውልደት እና መብዛት ጋር ተያይዞ የመጣ እሳቤ ነው፡፡ የቆየ ቀደም ሲል የሚነገር ቋንቋ ሳይሆን ከቅርብ አመታት ወዲህ በዓለም ላይ እየተነገረ የመጣ ቋንቋ ነው በእኛም ሀገር ከጠቀሜታው አንጻር ስታርት አፕ የሚሉ ቋንቋዎች በመጠኑም ቢሆን እየተነገሩ መጥተዋል፡፡

ብዙ ጊዜ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚፈጠሩ ሥራዎችን የሚፈጥሩት ሁለት እና ከዛ በላይ ሰዎች ናቸው የአፈጣጠር ባህሪው እራሱ የቡድን ሥራ በጋራ የመስራት ባህሪ እና ዝንባሌ አለው እስካሁን በታየው ልምድ አለም ላይ ስኬታማ የሆኑ ስታርት አፖች ዕድሜያቸው ከሠላሳ አምስት እስከ አርባ በአማካይ ያሉ ሰዎች ናቸው በስታርት አፕ የተሳካላቸው የሚባሉት፡፡

ስታርተ አፕ ላይ ለሚሳተፉ ሐሳብ አለን የሚሉ ትናንሽ ተቋማት መፍጠር እንችላለን ማደግ እንችላለን የሚሉ ወጣቶች ቢከተላቸው ብዬ የማስባቸውን ነገሮች …

ወጣቶች አራት የ“መ” መርህዎችን (ፕሪንሲፕል )ካላሟሉ በቀር ከ10% ስኬት የተጎናጸፉ ስታርት አፖች መካከል መሆን እይችሉም… አራቱን “መ” ካላሟሉ ከ90% መካከል ከማይሳካላቸው ነው የሚሆኑተ፡፡

አራቱ “መ” ምንድናቸው?

የመጀመሪያው ሊሰሩት ያሰቡትን ነገር ሐሳብ “መውደድ” ነው ፍቅሩ አላቸው? ወይ ይወዱታል ወይ? ምክንያቱም የምትወደው ነገር አያደክምህም የምትወደው ነገር አይስብርህም የምትወደው ነገር መከራን ቢያሸክምህም መከራ አይመስልህም ስለዚህ መጀመሪያ መውደድህን ማረጋገጥ አለብህ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ መውደድ ብቻውን በቂ አይደለም “መቻል’’ ያስፈልጋል ትችለዋለህ ወይ?

ለምሳሌ አውሮፕላን በአየር ላይ ሲሄድ አይተህ በጣም ደስ ይልሃል ግን አውሮፕላን መስራት እንደምትችል ካላሰብክ መተው ነው ያለብህ እኔ ሐሳብ አለኝ ምናምን ማለት የለብህም…

መውደድህን ቀጥሎ መቻልህን ማረጋገጥ አለብህ…

መውደድ እና መቻል በቂ አይደለም ሶስተኛው ስታርት አፕን ስኬታማ የሚያደርገው ነገር ‘’መፈለግ’’ ነው ።

ያ የምትወደው እና የምትችለው ነገር በማርኬቱ በገበያው በሕዝብ የፈለጋል ወይ? ገበያ አለው ወይ? ሰዎች የሚያደምጡት የሚፈልጉት የሚገዙት ነገር ነው ወይ? የሚለውን ማወቅ ያስፈልጋል።

አራተኛው ‘’መሸጥ’’ ነው ገንዘብ ማምጣት ነው።

መውደድ፣መቻል ፣መፈለግ፣መሽጥ ።